በቤይጀኢንግ የሚገኘውን የልዑካን ቡድን የሚመሩት የፓርቲችን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ ጠንካራ ፓርቲ ለመመስረት ጠንካራ የሥነ ምግባር እና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን የላቀ ሚና እንዳለው በመግለጽ፣ ከዚህ አንጻር ብልጽግና ፓርቲ የውስጥ ቁጥጥሩን ለማጠናከር በርካታ ስራዎችን መጀመሩንና ከዚህ አንጻር የረጅም ጊዜ ልምድ ካለው ሲፒሲ ተጨማሪ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
የሲፒሲ የሥነ ምግባር ኢንስፔክሽን ኮሚሽን አመራር የሆኑት ዋንግ ሺንቺ በሲፒሲ የውስጥ ኢንስፔክሽን አስፈላጊ የሆነበትን ምክንያት፣ የኮሚሽኑን ተግባራትና ሃላፊነቶች፣ ያከናወናቸውን ሥራዎች እና የአሰራር ሥርዓቱን በሚመለከት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አንድ ፓርቲ ለሕዝብ ለገባው ቃል ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥል እና በተለይም የአባላቱ ብዛትም ሆነ የፓርቲው መዋቅር እየሰፋ ሲሄድ ውጤታማነትን ከግልፅነትና ተጠያቂነት ጋር አስጠብቆ ለመቀጠል የውስጥ ሥነ ምግባርና ቁጥጥር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ክቡር አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው ብልጽግና ፓርቲ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ አባላትን በማፍራት መዋቅሩን እያስፋፋ መሆኑን በማንሳት አባላቱ በሥነ ምግባር ታንፀው ህዝብን እንዲያገለግሉ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም በጉባዔ የተመረጠና ከላይ እስከ ታች የተዋቀረ ጠንካራ የሥነ ምግባር እና የኢንስፔክሽን ኮሚሽን እየተገነባ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በልዑካን ቡድኑ አባላት በርካታ ሃሳቦች እና የማብራሪያ ጥያቄዎች ተነስተው ስፊ ውይይት ተደርጓል።
የአፍሪካ ከተሞች ፎረም በዛሬ ውሎ "የከንቲባዎች ሚና ለሌጋሲ ግቦች እና ለለውጥ አጀንዳዎች“ በሚል ርዕስ ከአህጉሪቱ ከተሞች ከተውጣጡ ከንቲባዎች፣ ኤክስፐርቶችን እና የአለምአቀፍ ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገናል::
ከተሞቻችንን በአግባቡ መምራት ከቻልን ሁለንተናዊ ልማት እዉን ለማድረግ እምቅ አቅሞች እንዳሉን እና በከተሞች ያለውን የድህነት አዙሪት መስበር፣ የተጎሳቆሉ አከባቢዎችን ማደስ፣ የአገልግሎትና መሰረተ-ልማትን ማስፋፋት፣ የመኖሪያ ቤት እጥረትን በቀጣይነት መፍታት የእኛ የከንቲባዎች አንገብጋቢ ስራዎች መሆናቸውን እንዲሁም የአመራርነት ተግዳሮቶችን ከመሰረታቸዉ በመፍታት ቅድሚያ የሚያሻቸዉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች መስራት እንዳለብን በውይይታችን ወቅት ተግባብተናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
የኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ሥራዎች እና የምግብ ሉዓላዊነት መንገድ በጠንካራ ትብብሮች ተሻግሮ ሀገራችን በአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ሳትበገር ራሷን ችላ ለምትቆምበት መፃዒ ተስፋ በር የሚከፍት ነው።
በዘላቂ የግብርና ሥራ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና የአቅም ግንባታ ሥራ ኢትዮጵያ ምርታማነትን ማላቅ፣ የአዝርዕት አይነትን ማብዛት ብሎም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ማሻሻል ትችላለች።
እንደዚህ አይነቶቹ ትብብሮች የማኅበረሰብን አቅም ከፍ ያደርጋሉ፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ይፈጥራሉ እንዲሁም ፈጠራን ያበረታታሉ። ይህም ኢትዮጵያን በዘላቂ የምግብ ሥርዓት መሪ ያደርጋታል፤ የበለፀገ የምግብ ዋስትና የተረጋገጠበት መፃዒ ጊዜንም ለህዝባችን ያረጋግጣል።
ዛሬ ከቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል።
ቀደም ብሎ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ላይ ከእኛ የዕድገት እና የልማት ግቦች ጋር የሚናበቡ ዐሥር ነጥቦች ያሉት የድርጊት መርሐ ግብር ይፋ አድርገዋል። በተለይም ያደገ ምርታማነትን ለማሳካት ሥራዎቻችንን በምናዘምንበት የግብርና ትብብር መንገድ ላይ ፍላጎታችንን ገልጫለሁ። በኢንዱስትሪ ልማት እና በዲጂታላይዜሽን ሥራዎቻችን ላይ ድጋፍ ስለምናገኝበት ሁኔታም ተወያይተናል።
በጋራ በተገኘንበት 17 የመግባቢያ ሰነዶች ተፈርመዋል። እነዚህ ስምምነቶች በኢትዮጵያ እና በቻይና ላለው በሁሉም ሁኔታ ለማይለዋወጠው ስትራቴጂያዊ ትብብር (all weather strategic cooperation partnership) ዓይነተኛ ማሳያ ናቸው።